Loading
Singer
እኔስ ፡ ቃሉን ፡ ስገልጠው ፡ የገረመኝ የእምነት ፡ አባት ፡ ስላለኝ ፡ ስላለኝ እኔስ ፡ ቃሉን ፡ ስገልጠው ፡ መንፈስ ፡ ነካኝ የእምነት ፡ አባት ፡ ስላለኝ ፡ ስላለኝ ብቻውን ፡ ቆሞ ፡ በአደባባይ ትወራረደ ፡ ጌታን ፡ ሊታይ በእሳት ፡ ተገልጦ ፡ አስደንቆታል የኤልያስ ፡ አምላክ ፡ እኔስ ፡ ገርሞኛል ቢወዳደሩ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋራ ፊት ፡ ብቧጥጡ ፡ በዓል ፡ ቢጠራ ሳይመጣ ፡ ቀርቶ ፡ ጉድ ፡ አረጋቸው አንድም ፡ ሳይቀሩ ፡ አስጨረሳቸው አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x) አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ አዋጁን ፡ ሽሬ አመልከዋለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ የማመልከዉ አዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ ሚያዘምር ፡ ነዉ (፪x) አኔማ ፡ አዋጅ ፡ ቢታወጅ ፡ እኔማ ፡ አዋጁን ፡ ሽሬ እኔማ ፡ አመልከዋለሁ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ክብሬ (፪x) አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x) መነሻም ፡ የለኝ ፡ ከተደፋሁ በዙፋኑ ፡ ሥር ፡ አመሻለሁ ፊቱ ፡ ወድቄ ፡ ተባረክ ፡ ስለዉ ይለቅልኛል ፡ መንፈሱን ፡ ሰማይ ፡ ክፍት ፡ ነዉ (፪x) እኔማ ፡ ማምለክ ፡ ጀምሬ ፡ እኔማ ፡ መቼ ፡ አቆማለሁ እኔማ ፡ የነካኝ ፡ ክብር ፡ እኔ ፡ ለየት ፡ ያለ ፡ ነው (፪x) አዝ:- ነገር ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) አለና ፡ ሚወጋ ፡ በጠላት ፡ ሰፈር ጩኸት ፡ አለኝ ፡ እኔስ ፡ ነገር ፡ አሃሃ (፪x) በሰባተኛው ፡ ቀን ፡ ይፈርሳል ፡ ቅጥር ይታመናል ፡ እግዚአብሔር ፡ ይታመናል (፬x)