Loading
Singer
አዝ፦ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፬x) በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ "ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ሺህ ፡ ዓመት ፡ ንገሥ !" የታመንኩት ፡ ጌታ ፡ ያድነኛል ፡ ያልኩት የአንበሶችን ፡ አፍ ፡ ቆልፎ ፡ አየሁት (፪x) ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ልንገርህ ፡ አምላኬ ፡ ጀግና ፡ ነው ተዓምርን ፡ ለማድረግ ፡ ለእርሱ ፡ ሁሉ ፡ ቀላል ፡ ነው ለጌታ ፡ ቀላል ፡ ነው [1] አዝ፦ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፬x) በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ "ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ልንገርህ ፡ ስማኝ !" ውስጤ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ያስቀመጠዉ በአስጨነቀህ ፡ ጉዳይ ፡ መፍትሄ ፡ በእኔ ፡ አለ (፪x) መቃብሬ ፡ ጉድጓድ ፡ በአንበሶች ፡ ማደሪያ በፍፁም ፡ አይሆንም ፡ አለው ፡ ብዙ ፡ ስራ (፪x) [2] አዝ፦ ነጋ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ (፬x) በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ እንደመሸ ፡ አልቀረም ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ በሰላም ፡ አደርኩኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ አንበሶች ፡ አልበሉኝ ፡ ሌሊቱ ፡ ነጋ ፡ ነጋ "ንጉሥ ፡ ሆይ ፡ ለአንዴና ፡ ለመጨረሻ ፡ ጊዜ ፡ አድምጠኝ !" ባለራዕይ ፡ ነኝ ፡ አልበላኝ ፡ አንበሳ ሰላም ፡ አድሪያለሁ ፡ በእርሱ ፡ የተነሳ ከጌታ ፡ የተነሳ አላሳፈረኝም ፡ የአመንኩት ፡ ጌታን ፡ ነው በላተኛው ፡ ትራስ ፡ ሆኖኝ ፡ አይቻለሁ (፪x) [1] የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ የሰራው ሌቱ ፡ ነግቶልኛል ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው የዳንኤል ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ይህን ፡ ያደረገው ሌቱ ፡ ነግቶልኛል ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው ባለራዕይ ፡ ነኝ ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው ውስጤ ፡ ነገር ፡ አለ ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው በፍፁም ፡ አልሞትም ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው ያወርሰኛል ፡ ገና ፡ ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው ተራው ፡ የእኔ ፡ ነው (፪x)