Loading
Singer
አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ በጎነቱ ፡ ሲነገረኝ ፡ ማዳኑ ፡ መቼ ፡ ማረከኝ ጆሮዬን ፡ በእጄ ፡ ዘግቼ ፡ ኢየሱስን ፡ አይን ፡ ላፈር ፡ አልኩኝ መራቡን ፡ ያላወቀ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ እንጀራ ፡ አንስቶ ፡ ይብላ ኋላ ፡ ግን ፡ ሲሞረሙረው ፡ ይሻዋል ፡ ቀድሞ ፡ እንዳልበላ አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ መስቀሉን ፡ በጀርባው ፡ ጭኜ ጦሬን ፡ መዝዤ ፡ ጨክኜ ጎልጎታ ፡ ድረስ ፡ ወሰድኩት እጁን ፡ ቸንክሬ ፡ ሰቀልኩት ከአዘነለት ፡ ሰው ፡ ይልቅ ፡ ምህረቱ ፡ ለኔ ፡ ቀደመ ሚያደርገውን ፡ አያውቅምና ፡ አባት ፡ ሆይ ፡ ማረው ፡ ተባለ አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ ኃጢያቴ ፡ በዝቶ ፡ በደጄ ፡ ሊገድለኝ ፡ ሲጥር ፡ ሲያደባ ባፈሰስኩበት ፡ ደሙ ፡ አጥቦ ፡ ሊያነፃኝ ፡ ቃል ፡ ገባ አጥንቴ ፡ ደቆ ፡ ስቆዝም ፡ አይዞህ ፡ የሚል ፡ ሰው ፡ ሲጠፋ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ለእኔ ፡ ደረሰ ፡ ያኔ ፡ በእጄ ፡ የተገፋ አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ አጥላልቼው ፡ ከወደደ ፡ ለሰቀልኩት ፡ ከማለደ ምን ፡ ይሆንለት ፡ ምላሹ ፡ እንደ ፡ ስራዬ ፡ ካላዋረደኝ ኢየሱሴ ፡ አድነኝ ፡ ስለው ፡ ያኔ ፡ ምን ፡ አረክ ፡ አላለም እንደ ፡ እርሱ ፡ ትሁት ፡ ቸር ፡ የለም ፡ ስሙ ፡ ይባረክ ፡ ዘላለም አዝ፦ በዘሬ ፡ አይግባ ፡ ያልኩት ከመንደሬ ፡ ገፍቼ ፡ ያወጣሁት እርሱ ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ ያዳንው በሞት ፡ መሃል ፡ የደረሰው ቀንበሬን ፡ የሰበረልኝ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ ኃጢያቴን ፡ ያልቆጠረብኝ ምህረቱን ፡ ያበዛልኝ ቸርነቱን ፡ ያወረደው ፡ ኢየሱስ ፡ ይባረክልኝ