Loading
Singer
አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x) ሊታይ ፡ በማይችል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ አለህ ሠማይ ፡ ምድርን ፡ በቃል ፡ ታዛለህ ወደደም ፡ ጠላም ፡ ፍጥረት ፡ በሙሉ ይገዛልሃል ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ኃይሉ አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x) ሰው ፡ ህልውናው ፡ ሞትና ፡ ሕይወቱ ሃዘን ፡ ደስታው ፡ ሹመት ፡ ሽረቱ ትእዛዝ ፡ ሁሉ ፡ ከአንተ ፡ ይወጣል ክብር ፡ ላንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል? አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x) እስከ ፡ እግርህ ፡ ጣት ፡ ዕንቁ ፡ ለብሰሃል ወገብህንም ፡ በወርቅ ፡ ታጥቀሃል ራስህ ፡ ነጭ ፡ ነው ፡ ዐይንህ ፡ ነበልባል ክብርም ፡ ስግደትም ፡ ላንተ ፡ ይገባል አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x) እግርህ ፡ በእቶን ፡ የነጠረ ፡ ናስ ድምፅህ ፡ ያስፈራል ፡ እንደ ፡ ውቅያኖስ የተሳለ ፡ ሰይፍ ፡ ከአፍህ ፡ ይወጣል ከቀትር ፡ ፀሐይ ፡ ፊትህ ፡ ያበራል አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x) ውለታህ ፡ በዝቶ ፡ ቢያስጨንቀኝ ያለኝን ፡ ሸጬ ፡ ሽቶ ፡ ገዛሁኝ ብልቃጡ ፡ ይሰበር ፡ ይፍሰስ ፡ በእግርህ እንዳከበርከኝ ፡ እኔም ፡ ላክብርህ አዝ፦ ነፍሴን ፡ በፊትህ ፡ አፈሳለሁ እጄን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አነሳለሁ ከመቀመጫዬም ፡ እወርዳለሁ ከእግሮችህ ፡ በታች ፡ እሰግዳለሁ አምላክ ፡ ነህና ፡ አመልክሃለሁ ንጉሥ ፡ ነህና ፡ አነግስሃለሁ (፪x)