Loading
Singer
ታስተማምናለህ ፡ ጌታዬ ፡ እኔም ፡ ታመንኩብህ ታስተማምናለህ ፡ ብቻህን ፡ እኔን ፡ ተደገፍኩብህ (፪x) ታምኜብሃለሁ ፡ ተደግፌሃለሁ ዘመኔን ፡ በሙሉ ፡ በአንተ ፡ እመካለሁ (፪x) አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x) የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x) ለምን ፡ እንደምኖር ፡ አውቃለሁ ፡ አንተን ፡ ስላገኘሁ ለሕይወቴ ፡ ትርጉምን ፡ ሰጥተሃል ፡ ልቤን ፡ አሳርፈሃል አርፌብሃለሁ ፡ ረክቼብሃለሁ ከቤትህ ፡ ጠል ፡ ጠጥቼ ፡ እኔስ ፡ እፎይ ፡ ብያለሁ (፪x) እግሮቼ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ቆመዋል እኔ ፡ አልናወጥም አረማመዴም ፡ ጸንቶልናል ፡ መሰረቴ ፡ አይወድቅም የማዕዘን ፡ ድንጋይ ፡ የሕይወቴ ፡ እራስ ብቃቴም ፡ ጉልበቴም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ኢየሱስ (፪x) አዝ፦ ነፍሴ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ፡ አንተን ፡ ታከብራለች በቀን ፡ በሌሊትም ፡ ትባርክሃለች (፪x) የመኖሬ ፡ ትርጉም ፡ የሕይወቴ ፡ መሰረት አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ የጸናሁብህ ፡ አለት (፪x)