Loading
Singer
አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ ፩) ኢየሱስ ፡ በፍቅሩ ፡ ወዶሻል ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ ከአብ ፡ አስታርቆሻል ታዲያ ፡ ለምን ፡ እረሳሽው ፡ ይህንን ፡ ውለታ ዘምሪለት ፡ እንጂ፡ ከጥዋት ፡ እስከ ፡ ማታ አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ ፪) ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ ሰባብሮ አንችን ፡ ግን ፡ መርጦሻል ፡ ጠላትን ፡ አባሮ አትቆጥቢ ፡ ተናገሪ ፡ የምስራቹን ፡ ቃል ላመኑት ፡ ሁሉ ፡ መጠጊያ ፡ ይሆናል አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ ፫) ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ታመኚ ባለውለታሽን ፡ እርሱን ፡ አመስግኝ ምህረቱ ፡ ለዘላለም ፡ አቁሞሻልና ማዳኑ ፡ ይነገር ፡ ዛሬም ፡ እንደገና አዝ፦ ነፍሴ ፡ ሆይ ፡ ዘምሪ ፡ ለወደደሽ ፡ ጌታ አንቺን ፡ ከገሃነም ፡ ከሲኦል ፡ ላወጣ እስኪ ፡ ድምጽሽን ፡ አሰሚ ኢየሱስ ፡ ያድናል ፡ እያልሽ ፡ ዘምሪ