Loading
Singer
አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x) ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ (፪x) ፍቅርህ ፡ ልቤን ፡ ከነካው ፡ ከለወጠው ሰንብቷል ፡ ያኔ ፡ ለጋ ፡ ሳለሁ ከውስጠቴ ፡ ዘልቆ ፡ ገብቶ ቤቱ ፡ አስቀረኝ ፡ ነፍሴን ፡ ማርኮ (፪x) አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x) ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ (፪x) ፀጋህና ፡ ምህረትህ ፡ ለመዳኔ ምክንያት ፡ ሆነኝ ፡ ለማምለጥ ፡ ከኩነኔ በመስቀል ፡ ላይ ፡ በሰራኀው ታላቅ ፡ ስራ ፡ እኖራለሁ በመስቀል ፡ ላይ ፡ በሰራኀው ታላቅ ፡ /ገድል ፡ ይሄው ፡ አለሁ አዝ፦ ነፍሴ ፡ አጥታልህ ፡ ለአንተ ፡ መግለጫ እንዲህ ፡ ትላለች ፡ ቢያረካህ ፡ ብላ (፪x) ሕይወቴ ፡ ያክብርህ ፡ በቀረው ፡ ዘመኔ ከእንግዲህ ፡ አይኑረኝ ፡ ምኖረው ፡ ለእኔ (፪x) ወደእግዚአብሔር ፡ የሚያደርሰው እውነት ፡ ሕይወት ፡ መንገድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው የሰው ፡ ልጅ ፡ በከንቱ ፡ እንዳይለፋ ሁሉን ፡ ፈጸመ ፡ ሰጠው ፡ ተስፋ የዳነ ፡ ሰው ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ በማንነቱ ከቶ ፡ አይደለም ፡ መወደዱ ፡ መመረጡ ዓለም ፡ ገና ፡ ሳይፈጠር ፡ በክርስቶስ የመረጠውን ፡ አጸደቀው ፡ አከበረው ማንም ፡ እንዳይመካ ፡ በስራው ፡ አይደለም ማንም ፡ እንዳይታበይ ፡ በስራው ፡ አይደለም (፪x)