Loading
Singer
ከሰማይ ፡ የመጣው ፡ የውዴ ፡ ውብ ፡ ቃል ልጄ ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ አንቺ ፡ የኔ ፡ ሲል በኮረብታዎች ፡ ላይ ፡ መጣልኝ ፡ ሲዘል ሐዘኔን ፡ ሊያስረሳ ፡ ነፍሴን ፡ ሊያባብል (፪x) አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ ወዳጄ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ ፡ ውበቴ ፡ ሆይ ፡ ነይ ክረምቱም ፡ አለፈ ፡ ብቅ ፡ አትይም ፡ ወይ አበቦች ፡ በምድር ፡ ይኸው ፡ ተገለጡ ወይኖችም ፡ አበቡ ፡ መዓዛቸውን ፡ ሰጡ በዓለት ፡ ንቃቃት ፡ ያለሽ ፡ እርግብ ፡ ሆይ ጊዜው ፡ ደርሷልና ፡ ነይ ፡ እንተያይ እያለ ፡ ሲያጽናናኝ ፡ ወዳጄ ፡ በቃሉ ነፍሴም ፡ ተነቃቃች ፡ እግሮቼም ፡ ዘለሉ አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ የሥጋና ፡ የደሜን ፡ የልቤን ፡ ትርታ የመንፈሴን ፡ ጩኸት ፡ የነፍሴን ፡ ሙግቷ ከወንድም ፡ አልጦ ፡ እኔን ፡ ሚጠጋጋ ወዳጅ ፡ አለኝና ፡ ለርሱ ፡ ብቻ ፡ ላውጋ ዘልቆ ፡ የሚያረሰርስ ፡ ቃል ፡ አለና ፡ ባፉ ሥሙን ፡ እየጠራሁ ፡ ልግባ ፡ ወደ ፡ እቅፉ ቃል ፡ ብቻ ፡ ይናገር ፡ እኔም ፡ እሰማለሁ ሸክሜን ፡ ሲያራግፈው ፡ ያኔ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ አዝ፦ የነፍሴ ፡ የውስጤ ፡ የልቤ ፡ የሚገባው ፡ ወዳጄ በቃሉ ፡ መጥቷል ፡ ወደ ፡ ደጄ ሲያንኳኳ ፡ ከፍቼ ፡ የክብርን ፡ ንጉሥ ፡ አስገባለሁ በአፉ ፡ ቃል ፡ ነፍሴን ፡ አጠግባለሁ