Loading
Singer
ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X በከፍታዎች ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ እስኪ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ ወንጭፌን ሞልቶታል ክብርና ምስጋና የጠላቴን አንገት ረግጫለሁና ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X ጌታዬን ታምኜ ጎልያድን ገጠምኩት በጭፍራዎቹ ፊት ጥዬ አዋረድኩት የለበሰው ብረት ለካ ከንቱ ነበር በአንዲት ጠጠር ብቻ ወድቆ የሚሰበር ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X የእስራኤል ተዋጊ ቅዱስ እግዚአብሔር በበረዶ ድንጋይ ጠላት የሚያባርር የእኔም ጌታ እርሱ ነው የሚሳነው የለም ዛሬም ለጠላቴ ወደኋላ አላለም ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው 2X የጠላቴን መንደር ለሚያወርሰኝ ጌታ እስኪ ላመስግነው ልዘምር በደስታ አትፍሪ እያለ ለሚያበረታኝ ለሚያከብረኝ ለእሱ ምስጋና አለኝ ምስጋና ነው በአፌ የሞላዉ ተትረፍርፏል ለአምላኬ ላፍስሰው X