Loading
Singer
እርቆ ፡ ለጠፋ ፡ ድርሻውን ፡ ይዞ ከአባቱ ፡ ቤት ፡ ኮብልሎ ፡ ወደ ፡ ምኞት ፡ ጉዞ እጅግ ፡ ክፉን ፡ ቢያደርግ ፡ ቢሆን ፡ ተላላ ነፍሱን ፡ አልጠቀመም ፡ ከፍቶታል ፡ በጣም አንድ ፡ ቀን ፡ ሲመለስ ፡ ወደ ፡ ልቡ ሀሳቡን ፡ ሰብስቦ ፡ ሲቃኝ ፡ አባቱን ይኖር ፡ ነበረ ፡ በደስታ ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ገብቶታል ፡ መሆኑ ፡ ጎስቋላ እንደ ፡ ልጁ ፡ ባያየኝ ፡ እንኳን ፡ ልሁን ፡ እንደ ፡ ባሪያ ብሎ ፡ ለወሰነ ፡ ለቆረጠ ፡ ጀግና ገና ፡ ሳይገባ ፡ ወደ ፡ መንደሩ ፡ አባቱ ፡ አቀፈው ፡ በፍቅር ፡ እጁ/ልክ ፡ እንደበፊቱ ና ፡ ና ፡ ና ፡ ጌታ ፡ ይወድሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ውዴ ፡ ይወድሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል ሁሉ ፡ እንዲመለስ ፡ በንስሀ ፡ ወዶ ፡ ይታገሳል ፡ ጌታ ዝምታው ፡ በኃጥያት ፡ አይደለም ፡ ማለት ፡ በርታ ቀን ፡ እጅግ ፡ ሳይከፋ ፡ ሳይመጣ ፡ የጥፋት ፡ ውሀ እንዳን ፡ በልጁ ፡ ግባ ፡ ወደ ፡ መርከቡ መርከብ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ማምለጫ ፡ መርከብ ወጀቡ ፡ ቢያልም ፡ ፍፁም ፡ አትሰጋበት ና ፡ ና ፡ ና ፡ ጌታ ፡ ይወድሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ውዴ ፡ ይወድሀል ና ፡ ና ፡ ና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ይጠራሀል ቢጠላ ፡ እንጂ ፡ ሀጥያትን ፡ ኃጥያተኛን ፡ ከልቡ ፡ ይወዳል ይሉት ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ቀድሞም ፡ እርሱ ፡ ከአመጸኞች ፡ ጋር ፡ ይወዳጃል መሪ ፡ አጥተው ፡ ለተበተኑ ፡ እውነተኛ ፡ እረኛ ፡ ነው ይሰበስባል ፡ በፍቅር ፡ እጁ ፡ አቅፎ ፡ ያሞቃል ፡ በእቅፉ