Loading
Singer
ሕዝብህ ፡ ይጠብቅሃል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! መገለጥህ ፡ ናፍቆታል ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! እባክህ ፡ ናልኝ ፡ ሳትቆይ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ ? ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x) ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ? ስምህን ፡ ስለወደደች ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ነፍሴ ፡ ስድብን ፡ ጠገበች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታዬ ፡ ሆይ! ባርኮቷን ፡ እያሰበች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ዛሬም ፡ በአንተ ፡ ታምናለች፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x) ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ? ድካሙ ፡ ሳይበረታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! አርበኛው ፡ ሳይረታ፡ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! የተጋዳይ ፡ አለኝታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! በጠላትህ ፡ ላይ ፡ በርታ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x) ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ? ጣኦቱ ፡ ተሰባብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ልመልከት ፡ ስምህ ፡ ከብሮ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ከጥንት ፡ እንደታወቅህ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! ምድር ፡ አንተን ፡ ትወቅ ፣ ና ፣ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! አዝ፦ ና ፡ ጌታዬ ፣ ጌታ ፡ ሆይ! (፫x) ጊዜው ፡ አልደረሰም ፡ ወይ?