Loading
Singer
አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ የቃልኪዳን አምላክ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ (አሜን) ፡ ልዑል ፡ አሰናዳ ፤ (አሜን) ፡ ባርኮት ፡ የሚበላ (አሜን) ፡ ከማመስገን ፡ በቀር ፤ (አሜን) ፡ ምን ፡ ይባላል ፡ ሌላ (አሜን) ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ፤ (አሜን) ፡ ወደ ፡ እረፍት ፡ አመጣን (አሜን) ፡ ከብቸኝነቱ ፤ (አሜን) ፡ መንደር ፡ እያወጣ አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ (አሜን) ፡ አክሊል ፡ የለበሰ ፤ (አሜን) ፡ ሙሽራው ፡ ሲያምርበት (አሜን) ፡ በጌጥ ፡ ሽልማቷ ፤ (አሜን) ፡ ሙሽሪት ፡ ሲያምርባት (አሜን) ፡ ነገር ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፤ (አሜን) ፡ ጽድቅን ፡ አጐናጽፎ (አሜን) ፡ ሰውን ፡ ለዚህ ፡ ያበቃል ፤ (አሜን) ፡ ሁሉን ፡ አሳልፎ አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ አዲስ ፡ ጐጆ ፡ ወጪ ፡ በይ ፡ ባርኮቱን ፡ ጠጪ ብሎ ፡ የመረቃት ፡ ደጉ ፡ ቸሩ ፡ አባት እረድቷት ፡ አምላኳ ፡ ሲለወጥ ፡ ታሪኳ ጐጆን ፡ ማን ፡ አስወጣት ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ያገዛት (፪x) ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ምህረቱ ፡ የጌታ በእርሱ ፡ ተጀምሯል ፡ የሙሽሪት ፡ ቤቷ (፬x) አዲስ ፡ ስፍራ ፡ ሰጥቶ ፡ በኑሮም ፡ ገብቶ ጌታ ፡ አደላደለው ፡ ተመስገን ፡ አስባለው ይህን ፡ ሁሉ ፡ ነገር ፡ ስላሳየን ፡ ይክበር ቃሉን ፡ ላላጠፈው ፡ ምሥጋናችን ፡ ይሄው (፪x) ምህረቱ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ በእርሱ ፡ ተጀምሯል ፡ የሙሽራው ፡ ቤቱ (፬x) (አሜን) ፡ ፍቅር ፡ ግን ፡ እስከሞት ፤ (አሜን) ፡ ብርቱ ፡ ስለሆነ (አሜን) ፡ እርሷም ፡ ለእርሱ ፡ ሆነች ፤ (አሜን) ፡ እርሱም ፡ ለእርሷ ፡ ሆነ (አሜን) ፡ ጌታ ፡ ያነደደውን ፤ (አሜን) ፡ የፍቅርን ፡ እሳት (አሜን) ፡ ብዙ ፡ የጥፋት ፡ ውኃ ፤ (አሜን) ፡ አይችልም ፡ ሊያጠፋት አዝ፦ ሙሽሪት ፡ ሙሽራው ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላቹህ የቃልኪዳን ፡ አምላክ ፡ ያስተሳሰራቹህ እግዚአብሔር ፡ ነውና ፡ የትዳር ፡ ጅማሬ ኦ ፡ ስራው ፡ ግሩም ፡ ነው ደስ ፡ ብሎናል ፡ ዛሬ