Loading
Singer
የልዑሉ ፡ አምላክ ፡ ማደሪያ አካሉ ፡ የሆንሽ ፡ የእርሱ መኖሪያ አንች ፡ ቤተክርስቲን ፡ ተነሺ የሰጠሽን ፡ ተስፋ ፡ አትርሺ ሁኝ ፡ እንጂ ፡ ልክ ፡ እንደ ፡ ሙሽራ ልትቆሚ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ በተራራ የሰርግሽ ፡ ቀን ፡ በጣም ፡ ቅርብ ፡ ነው ሙሽራሽ ፡ ደጂ ፡ እያንኳኳ ፡ ነው ዘምሪለት ፡ እንጂ ፡ በዕልልታ የምን ፡ በራድ ፡ ትኩስ ፡ ለብታ ድመቂ ፡ ንሺ ፡ ተቀደሽ ሙሽራይቱ ፡ ሆይ ፡ ተነሽ መቅረዝሽ ፡ በዘይት ፡ ይሞላ በር ፡ እንዳይዘጋብሽ ፡ ኋላ ቀን ፡ ሳላ ፡ ዛሬ ፡ ተዘጋጂ በፍጻሜው ፡ እንዳትጐጂ ረሻሽ ፡ ወይ ፡ ጌታሽ ፡ መመለሱን ጠብቂኝ ፡ እመጣለህ ፡ ማለቱን መዘናጋቱ ፡ ምነው ፡ በዛ ጣል ፡ እረግሽው ፡ ልክ ፡ እንደዋዛ የወደፊቱ ፡ ክብር ፡ ተስፋ ተጋረደ ፡ ከዓይንሽ ፡ ስር ፡ ጠፋ ጊዜው ፡ ደርሷል ፡ እባክሽን ፡ ንቂ ቤተክርስቲያን ፡ ተጠንቀቂ ሊያደርግሽ ፡ ፍሬ ፡ አልባ ፡ ገለባ የዓለም ፡ ኮተት ፡ ሰርጐ ፡ ገባ ተኝተሽ ፡ ጠላት ፡ ዘሩን ፡ ዘራ ምድርሽ ፡ እንክርዳድን ፡ አፈራ በበጉ ፡ ደም ፡ ፈጥነሽ ፡ ታጠቢ አስታውሺ ፡ ተስፋሽን ፡ አስቢ የሰርጉ ፡ ቀን ፡ በጣም ፡ ተቃርቧል ሙሽራሽ ፡ ወደ ፡ አንቺ ፡ ይመጣል አሜን ፡ ማራናታ ፡ ቶሎ ፡ ና የምትይበት ፡ ጊዜው ፡ ነውና ይሰማ ፡ ድምፅሽ ፡ ያስተጋባ ወደ ፡ ልዑል ፡ ማደሪያ ፡ ይግባ ከእንግዲህ ፡ በምድር ፡ ምን ፡ ቀረሺ ናፍቂ ፡ ወደሰማይ ፡ ገስግሺ ይልቃል ፡ በዚያ ፡ ያለው ፡ ደስታ ማሰማት ፡ ዝማሬና ፡ ዕልልታ በዚያ ፡ እኮ ፡ ርሃብ ፡ ጥማት ፡ የለም ደዌ ፡ ህመም ፡ አይታወቅም እንባ ፡ ከዓይኖችሽ ፡ ይታበሳል በጉ ፡ የአንች ፡ እረኛ ፡ ይሆናል የበጉ ፡ መሽራ ፡ አንቺ ፡ ሆይ ይህ ፡ ክበር ፡ አልናፈቀሽም ፡ ወይ ይመጣል ፡ ወዳጅሽ ፡ ወደ ፡ አንቺ ተነሽ ፡ ቁሚ ፡ ተዘጋጂ ማራናታ ፣ ማራናታ አሜን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተሎ ፡ ና አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተሎ ፡ ና አሜን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ተሎ ፡ ና አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተሎ ፡ ና (፪x)