Loading
Singer
ጠልቄ ፡ መሄድ ፡ እፈልጋለሁ የእኔ ፡ እርካታ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው ላይ ፡ ላዩን ፡ መሄድ ፡ ይቅርብኝና ይስጠም ፡ ሕይወቴ ፡ በህልውና (፪x) መንፈስ ፡ ቅዱስ (፪x) አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x) ላንብብ ፡ ቃልህን ፡ ልስማ ሕግህን ላድርግ ፡ ስራዬን ፡ ደስ ፡ የሚልህን መቅደስነቴ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው የለኝም ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ ደባል ፡ የማደርገው ከምር ፡ ነው ፡ ከልብ ነው የአንተ መሆን ምፈልገው ማንከስ ፡ ይቅር ፡ በሃሳቤ ልከተልህ ፡ ቆርጦ ፡ ልቤ አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x) እኔ ፡ ግን ፡ እኔ ግን (፪x) በጽድቅህ ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ ክብርህን ፡ ሳይ ፡ እጠግባለሁ (፪x) ቁርጭምጭሚት ፡ ጋ ፡ ባለው ፡ ሕይወቴ በቃኝ ፡ አልበል ፡ በዚህ ፡ ረክቼ ጉልበቴን ፡ እና ፡ ወገቤን ፡ አልፈህ ተቆጣጠረኝ ፡ ከሁሉ ፡ ልቀህ በአንተ ፡ ተይዞ ፡ ሁሉ ፡ ነገሬ ቢያልቅ ፡ ይሻላል ፡ ቀሪ ፡ ዘመኔ ጠልቄ ፡ መሄድ ፡ እፈልጋለሁ የእኔ ፡ እርካታ ፡ የአንተ ፡ ክብር ፡ ነው ላይ ፡ ላዩን ፡ መሄድ ፡ ይቅርብኝና ይስጠም ፡ ሕይወቴ ፡ በህልውናህ (፪x) መንፈስ ፡ ቅዱስ (፪x) አዝ፦ ሙላኝ ፡ ተቆጣጠረኝ ሌላ ፡ ሕይወት ፡ አይኑረኝ (፬x)