Loading
Singer
አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል (፪x) የዓለም ፡ መድኃኒት ፡ ይሄን ፡ ትሁት ቢደፋ ፡ አንገቱን ፡ ቀላል ፡ አርገውት እውር ፡ ሲያበራ ፡ ዲዳ ፡ ሲያናግር በክፉ ፡ አናት ፡ ላይ ፡ እሳት ፡ ሲጭር ተደንቀው ፡ አዩት ፡ ኧረ ፡ ይሄስ ፡ ማነው አውሎ ፡ ንፋሱን ፡ ወጀቡን ፡ የሚያዘው አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል ትክክለኛ ፡ ሰራተኛ ሽንገላ ፡ የሌለበት ፡ እውነተኛ ሃሰተኞች ፡ ቢያደናብሩ ቃሉን ፡ በተንኮል ፡ ቢመነዝሩ ልቡ ፡ አይደነግጥ ፡ ምንም ፡ ቢሆን ፡ አይፈራ በአደባባይ ፡ በግልጥ ፡ አለ ፡ እየሰራ አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል ያንበረከከ ፡ መተተኞችን በሰው ፡ ላይ ፡ የሚጫወቱ ፡ ጠንቋዮችን ጓዛቸውን ፡ ጥለው ፡ ፈረጠጡ በቁጣው ፡ ጅራፍ ፡ እየተቀጡ ጌታ ፡ ነን ፡ ያሉ ፡ የታል ፡ አቅማቸው ወድቀው ፡ ቀሩ ፡ እንጂ ፡ ሲነሱ ፡ አላየናቸው አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል ወረት ፡ መስሏቸው ፡ የነገራቸው በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ እነሳለሁ ፡ ሲላቸው መሳቂያ ፡ አደረጉት ፡ መሳለቂያ ምን ፡ ልታመጣ ፡ ከእንግዲህ ፡ ወዲያ የጠበቃት ፡ ቀን ፡ ደረሰችና አናወጣቸው ፡ ከሞት ፡ ተነሳና አዝ፦ ሞትን ፡ የረታ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የምናመልከው የዲያቢሎስን ፡ ክፉ ፡ ሥራ ፡ ያፈረሰው አልተሸነፈም ፡ አይሸነፍም ፡ አይተነዋል አምላካችንን ፡ ንጉሣችንን ፡ ማን ፡ ይመስለዋል (፪x)