Loading
Singer
ሞት ፡ መሻገሪያዬ ወደ ፡ ዘላለም ፡ ቤት ፡ ማለፊያዬ የናፈቁትን ፡ የምወርስበት አምላኬን ፡ የማገኝበት የዘላለም ፡ ቤት ፡ መግቢያዬ ሞት ፡ መሻገሪያዬ (፪x) የእኔ ፡ ኑሮ ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ አያበቃም ቆይታዬ ፡ መጨረሺያዬ ፡ በዚህ ፡ አይደለም ይቀጥላል ፡ ከሞት ፡ ወዲያ ፡ በአዲስ ፡ ሕይወት በዘለዓለም ፡ ቤት ፡ በደስታዬ ፡ ቤት (፪x) ምኞቴን ፡ አይደለም ፡ የምናገረው በእርግጥ ፡ የሚሆን ፡ የሚታይ ፡ ነው በቃሉ ፡ እንደገባልኝ ፡ ቃል ፡ ኪዳን ከሞት ፡ ወዲያ ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ እንደምሆን ፡ ነው (፪x) ሞትን ፡ ድል ፡ ነስቶልኛል እንዴት ፡ ውጦ ፡ ያስቀረኛል ተሻግሯል ፡ አልፏል ፡ ኑሮዬ አልቀርም ፡ በሞት ፡ ተይዤ ሞት ፡ ለእኔ ፡ ጥቅሜ ፡ ነው ሞት ፡ ለእኔ ፡ ክብሬ ፡ ነው (፪x)