Loading
Singer
አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x) የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱሴ የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ ዛሬ ፡ ላየኝ ፡ ላስተዋለኝ ፡ ሰው እኔ ፡ አልለውም ፡ እጄ ፡ አንዳረገው እናገራለሁ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ብዬ አልደብቀውም ፡ ኢየሱስዬን እርሱ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ሞገስ ፡ የሆነኝ ከአፈር ፡ አንስቶ ፡ ክብር ፡ ያሳየኝ ታናሹን ፡ ሰው ፡ ሊያከብረኝ ፡ ወዶ ቤቴ ፡ ገባ ፡ ከሰማይ ፡ ወርዶ በዓይኖችህ ፡ ከታየሁኝ ፡ እኔ ፡ እጆችህ ፡ ከያዙኝ ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ እሰጋለሁ አንተን ፡ ይዣለሁ አንተን ፡ ያስቀደመ ፡ ሰው አይጐልም ፡ ከሚያስበው ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ ይሰጋል አንተን ፡ ይዞሃል አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x) የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ ማዕረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱሴ የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ ምሕረቱ ፡ የረዳው ፡ ሰው ቸርነቱ ፡ ሰው ፡ ያረገው እኔ ፡ ነኝ ፡ ያ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ በፍቅሩ ፡ የታደገኝ አቅም ፡ አጣሁ ፡ ጉልበቴ ፡ ጠፋ እኔስ ፡ የለኝም ፡ የመኖር ፡ ተስፋ ብሎ ፡ ለሚል ፡ ጌታ ፡ አለው ፡ መላ ታሪክ ፡ ከፍቶ ፡ ያሳያል ፡ ሌላ በዓይኖችህ ፡ ከታየሁኝ ፡ እኔ ፡ እጆችህ ፡ ከያዙኝ ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ እሰጋለሁ አንተን ፡ ይዣለሁ አንተን ፡ ያስቀደመ ፡ ሰው አይጐልም ፡ ከሚያስበው ከዚህ ፡ ወዲያ ፡ በምን ፡ ይሰጋል አንተን ፡ ይዞሃል አዝ፦ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ (፪x) የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ ማረጌ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ የእኔ ፡ ኢየሱሴ የማልተካው ፡ የማልተወው ፡ በሕይወቴ