Loading
Singer
ሚስጥርን ፡ የሚገልጥ ፡ በሰማይ ፡ ውስጥ ፡ አለ ዙፋኑ ፡ በብዙ ፡ ክብር ፡ የተከለለ ከሰው ፡ ልብ ፡ የጠፋን ፡ ህልም ፡ ከነፍቺው የሚያቀብል ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ዙፋኑ ፡ በሰማይ ፡ ርቆ ፡ ከፍ ፡ ቢልም በዓይኖቹ ፡ ከማየት ፡ ፍፁም ፡ አይታክትም የተሰወረውን ፡ በታች ፡ በሸለቆ እርሱ ፡ ወደ ፡ ብርሃን ፡ ይገልጠዋል ፡ አውቆ (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ከፊቱ ፡ የሚሰወር ማነው ፡ ከእርሱ ፡ የሚደበቅ ማነው ፡ ወጥቶ ፡ የሚገባ ማነው ፡ አምላኬ ፡ ሳያውቅ ያያል ፡ ያያል ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያያል ያውቃል ፡ ያውቃል ፡ አስተውሎ ፡ ያውቃል ዝም ፡ ቢል ፡ ቢታገስ ፡ ለፍርድ ፡ ባይቸኩል የተወህ ፡ የረሳህ ፡ ያላየህ ፡ አይምሰልህ (፪x) የቀድሞውን ፡ ዘመን ፡ ወይንም ፡ የአሁኑ ገና ፡ የሚመጣውን ፡ የወደፊቱን የፍጥረትን ፡ ሩጫ ፡ ሙሉ ፡ እንቅስቃሴ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል ፡ አምላኬ ፡ ንጉሤ (፪x) ነገር ፡ ሁሉ ፡ ፊቱ ፡ ዕርቃኑን ፡ ይቆማል ማን ፡ ከእርሱ ፡ ሚስጥሩን ፡ ደብቆ ፡ ያኖራል የሰማይ ፡ የምድሩን ፡ ሁሉንም ፡ አዋቂ ከስውርም ፡ ወጥመድ ፡ አዳኝ ፡ ነው ፡ ነጣቂ (፪x) አዝ፦ ማነው ፡ ከፊቱ ፡ የሚሰወር ማነው ፡ ከእርሱ ፡ የሚደበቅ ማነው ፡ ወጥቶ ፡ የሚገባ ማነው ፡ አምላኬ ፡ ሳያውቅ ያያል ፡ ያያል ፡ ሁሉን ፡ ነገር ፡ ያያል ያውቃል ፡ ያውቃል ፡ አስተውሎ ፡ ያውቃል ዝም ፡ ቢል ፡ ቢታገስ ፡ ለፍርድ ፡ ባይቸኩል የተወህ ፡ የረሳህ ፡ ያላየህ ፡ አይምሰልህ (፪x)