Loading
Singer
በተጣለች አለም - መሃል የዘመትን የምንለመልም - ዘዉትር እየሞትን ትውልድን ለማትረፍ - ከዘላለም ቁጣ የመዳንን ወንጌል - ይዘን የምንወጣ… (ምስክር ነን እኛ!) - [አዝ] ጥበባችን ሁሉ - ሞኝነት ‘ሚመስል የእግ’ዚአብሔርን ፍቅር - ለሰው የምንስል ሲረግሙን መራቂ - ላሳዳጆች ፀላይ መልካም የምንመኝ - ጠላቶቻችን ላይ… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] ዋጋችን በሰማይ - ሀይላችን በፀሎት ምንዳን የማንሻ - ለምድር አገልግሎት ኢየሱስን ይዘን - የማናቀረቅር መንገዳችን ቀና - እርምጃችን ፍቅር… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] “የምን ደርሶ አዋቂ - የምን ደርሶ አቡን አጉል ጠበቃዎች…” - ሲሉ ቢያዋክቡን ቢያላጉን በጥፊ - ቢያዳፉን በጡጫ በስል ምላሳቸው - ብንሆን ማላገጫ… ምስክር ነን እኛ! [አዝ] በሞት ጥላ ግርዶሽ - ተከበው ለኖሩ ብቃት አጣን ብለው - አጋዥ ለሚጠሩ የምስራች ይዘን - ለህዝቡ ወጥተናል ዛሬም እንላለን - ኢየሱስ ያድናል!! (ኢየሱስ ያድናል)