Loading
Singer
ምስጋና ነው ባፌ የሞላው ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው በከፍታዋች ላይ ለሚያቆመኝ ጌታ እስቲ ላመስግነው ልዘምር በእልልታ ወንጭፌን ሞልቶታል ክብርና ምስጋና የጠላቴን አንገት ረግጫለሁና ምስጋና ነው ባፌ የሞላው ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው ጌታዬን ታምኜ ጎልያድን ገጠምኩት በጭፍራዎቹ ፊት ጥዬ አዋረድኩት የለበሰው ብረት ለካ ከንቱ ነበር ባንዲት ጠጠር ብቻ ወድቆ የሚሰበር ምስጋና ነው ባፌ የሞላው ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው የእስራኤል ተዋጊ ቅዱስ እግዚአብሔር በበረዶ ድንጋይ ጠላቴን ሚያባርር የኔም ጌታ እርሱ ነው የሚሳነው የለም ዛሬም ለጠላቴ ወደኋላ አላለም ምስጋና ነው ባፌ የሞላው ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው የጠላቴን መንደር ለሚያወርሰኝ ጌታ እስቲ ላመስግነው ልዘምር በደስታ አትፍሪ እያለ ለሚያበረታኝ ለሚያከብረኝ ለእርሱ ምስጋና አለኝ ምስጋና ነው ባፌ የሞላው ተትረፍርፏል ላምላኬ ላፍሰው