Loading
ኦሆሆሆ (፫x) እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ግርማህ ፡ አስፈሪ የሌለህ ፡ አቻ ፡ ተወዳዳሪ ፡ ሆሆ ፡ ተወዳዳሪ በትረ ፡ መንግሥትህ ፡ በዓለም ፡ የታወቀ እንዳንተ ፡ ማነው ፡ ሁሉን ፡ የበለጠ ሆሆ ፡ ከሁሉም ፡ የላቀ (፪x) ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ ምድር ፡ መርገጫህ ለግዛትህ ፡ ወሰን የሌለህ ፡ ዳርቻ ልዑል ፡ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ልዑል ፡ ከፍ ፡ ያለው ፡ ዙፋንህ አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ (፪x) ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ሥምክን ፡ ያድምቀው (፪x) ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከ ፡ ጫፍ ፡ ቢሰበሰብ ፡ ፍጥረት የሰማይ ፡ ሰራዊት ፡ እልፍ ፡ ጊዜ ፡ አላፋት ሁሉም ፡ ተሰብሰቦ ፡ ስለ ፡ አንተ ፡ ቢያወራ ሊገልፅህ ፡ ቢሞክር ፡ በተራ ፡ በተራ ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ (፪x) ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ ምድር ፡ መርገጫህ ለገዛትህ ፡ ወሰን የሌለህ ፡ ዳርቻ ልዑል ፡ ለትልቅነትህ ልዑል ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ሥምህን ፡ ያድምቀው (፪x) አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x) አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x) አቻ ፡ አጣሁልህ ፡ ወደር ፡ አጣሁልህ መሳይ ፡ አጣሁልህ ፡ እኩያ ፡ አጣሁልህ (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስልህ (፬x) አንተ ፡ የከበርክበት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያልክበት የላቀ ፡ ሥልጣንህ ፡ ማነው ፡ የደረሰበት ወልድ ፡ የተረከህ ፡ ሆይ ፡ ስለ ፡ ማንነትህ ፅድቅ ፡ ነው ፡ ዙፋንህ ፡ ብርሃን ፡ አልባሳትህ ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ ምሳሌ ፡ የሌለህ ፡ ነህ ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ (፪x) ልዑል ፡ ሰማይ ፡ ዙፋንህ ምድር ፡ መርገጫህ ለገዛትህ ፡ ወሰን የሌለህ ፡ ዳርቻ ልዑል ፡ ለትልቅነትህ ልዑል ፡ ምሳሌ ፡ የሌለህ አምልኮና ፡ ስግደት ፡ ይሁንልህ ይብዛልህ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ላብዛልህ ፡ ዕልልታዬ በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ሥራዬ ፡ ይኸው ምሥጋናዬ ፡ ዙፋንህን ፡ ይክበበው አምልኮዬ ፡ ክቡር ፡ ስምህን ፡ ያድምቀው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.