Loading
Singer
መዝሙር ፡ አልቀይርም ፡ ቃሌ ፡ ቃል ፡ ነውና መልካምነትህን ፡ ዘምሬይለሁና ሲሆን ፡ ተደስቼ ፡ ሳይሆን ፡ ተከፍቼ አላማህም ፡ ጌታ ፡ እኔ ፡ አፌን ፡ ሞልቼ ዛሬም ፡ እላለሁ ፡ እንዲህ ፡ እላለሁ የሕይወት ፡ ራስ ፡ ነህ ፡ ንጉሤ ፡ አልሃለሁ (፪x) የሕይወት ፡ ራስ ፡ ነህ ራስ ፡ ለቤቴ ተመስገንልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ (፪x) ያልደምከምኩበትን ፡ ሕይወት ፡ ሰጥተኸኛል እንዳገለግልህ ፡ እድል ፡ ሰጥተኸኛል እርግማኔን ፡ ባርኮት ፡ አርገህ ፡ የቀየርክ ፍጻሜዬ ፡ በሃዘን ፡ እንዳይዘጋ ፡ ነው አልቀለለብኝም ፡ ክቡር ፡ ነው ፡ መዳኔ ምሥጋናን ፡ ባበዛ ፡ ሲያንስብኝ ፡ ነው ፡ እኔ የጥረቴ ፡ ድካም ፡ ሳታደርግብኝ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ኢየሱስ ፡ አዳንከኝ አዳንከኝ ፡ ኦ ፡ የማንም ፡ እጅ ፡ የለበትም ስለመዳኔ ፡ ስለመትረፈ ተመስገንልኝ ፡ አባዬ