Loading
Singer
የልቤ ፡ አፅናኝ አይዞህ ፡ ምትለኝ ከሞት ፡ አውጥተኸኝ ህያው ፡ ያረከኝ አዝ፦ መፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ በጣፋጩ ፡ ዜማ ፡ ቃላትን ፡ መርጬ በመንፈስ ፡ ማደሪያ ፡ ወዳንተ ፡ ገብቼ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ላንተ ፡ ያለውን ፡ አክብሮት ፡ ይገልጣል እንዲህ ፡ ይልሃል አዝ፦ መፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ ሁሉን ፡ የምትገዛ ፡ ጌታ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ በጥላህ ፡ አርፌ ፡ ብያለሁኝ ፡ እፎይ ከስትንፋስ ፡ የሚቀርብ ፡ የለኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ የልቤ ፡ መበርቻ ፡ መፅናኛ ፡ ከለላ የልቤ ፡ አፅናኝ አይዞህ ፡ ምትለኝ ከሞት ፡ አውጥተኸኝ ህያው ፡ ያረከኝ አዝ፦ መፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ ካእላፋት ፡ መሀል ፡ እንዴት ፡ ትዝ ፡ እንዳልኩህ ማን ፡ ሆኜ ፡ አዳንከኝ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ ጠየኩህ አንተም ፡ መለስክልኝ ፡ በጣፋጩ ፡ ቃልህ ፍቅር ፡ እንደሆነ ፡ ለኔ ፡ ግድ ፡ ያስባለህ በጣፋጩ ፡ ዜማ ፡ ቃላትን ፡ መርጬ በመንፈስ ፡ ማደሪያ ፡ ወዳንተ ፡ ገብቼ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ይኸው ፡ ልቤ ፡ ለአንተ ፡ ያለውን ፡ አክብሮት ፡ ይገልጣል እንዲህ ፡ ይልሃል አዝ፦ መፅናኛዬ (፫x) ፡ አንተ መበርቻዬ (፫x) ፡ አንተ