Loading
Singer
እንደ ፡ እናት ፡ ነህ ፡ አልልም እንደ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ አልልም ምትክ ፡ የለህ ፡ መድህኔ አንድ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x) አንድ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ የለኝም ፡ የማቆመው/የምተካው ፡ በአንተ ፡ ቦታ (፪x) አንዱ ፡ ሲመጣ ፡ አንዱ ፡ ይሄዳል በምድር ፡ ያለው ፡ ይቀያየራል ኢየሱሴ ፡ ካንተ ፡ የተለየ ፡ ሰው ባንተ ፡ ቦታ ፡ የሚቆምለት ፡ ማነው (፪x) አንተ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አንተ ፡ ማን ፡ ሊተካ አንተ ፡ የእኔ ፡ አምላክ አንተ ፡ የለም ፡ ምትክ (፪x) ለእኔስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መሪዬ የቅርቡ ፡ ተጠሪዬ የቅርቡ ፡ ተጠሪዬ (፪x) ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማነዉ (፪x) ከአንተስ ፡ ሌላ ፡ ለእኔስ ፡ ለምኔ (፪x) ፍቅርህ ፡ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ይጣፍጣል (፪x) ፍቅርህ ፡ ከማር ፡ ወለላም ፡ ይመረጣል (፪x) ይመረጣል ፡ አሃሃ ፡ ይመረጣል (፪x)