Loading
Singer
እንውጣ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ አንጨዋወት ወንድማማቾች ፡ ነን ፡ የአንድ ፡ እናት ፡ አባት አባብሎ ፡ አባብሎ ፡ ይዞ ፡ አወጣና ወንድሙን ፡ ገደለው ፡ ቃየል ፡ ጨከነና [1] የገርማል ፡ ይገርማል የዘንድሮ ፡ ቃየል ፡ ሲችልበት ፡ ማስመሰል (፪x) ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ፈራሁኝ ፡ ለእራሴ ከእንዲህ ፡ ዓይነቱ ፡ ሰው ፡ ጠብቀኝ ፡ ኢየሱሴ እንዴት ፡ ተሳካለት ፡ እንዴት ፡ ጥሶ ፡ ወጣ እንዴት ፡ አሸተተው ፡ መሷዕቱን ፡ ጌታ ብሎ ፡ የሚቆታ ፡ ሰው ፡ ከገጠማችሁ ኋላ ፡ ነፍስ ፡ ያተፋል ፡ መልሱት ፡ ባካችሁ መልሱት ፡ ባካችሁ ፡ ምከርቱት ፡ ባካችሁ (፪x) ክፉ ፡ ቀን ፡ አለ ፡ ደግ ፡ ቀን ፡ አለ ባንተዛዘል ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አለ ጠባቂ ፡ እንሁን ፡ ለወንድማችን አይቀርምና ፡ መጸጸታችን እኔማ ፡ ቃልህ ፡ ይሻለናል እኔማ ፡ የሚል ፡ ና ፡ ተመለስ እኔማ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ለመንገሥ እኔማ ፡ ሕይወት ፡ ይሻለኛል እኔማ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ለመንገሥ