Loading
Singer
መታመኛዬ ፡ መታመኛዬ እግዚአብሔር ፡ በዙፋኑ ፡ አለ ሁሉንም ፡ አዲስ ፡ የሚያደርገው ቀን ፡ ቀጥሮ ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ የሚል ታሪክን ፡ በታሪክ ፡ ሚሽረው ጌታ ፡ ነው ፡ የሁሉ ፡ ቁልፍ ፡ ያለው ጌታ ፡ ነው ፡ እኔ ፡ ምታመነው ጌታ ፡ ነው ፡ ድንገት ፡ ከተፍ ፡ የሚል ጌታ ፡ ነው ፡ ሁሉ ፡ የሚቻለው ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ ፡ በአንተ ፡ ተማምኜ (፪x) እጅግ ፡ በሚመቸው ፡ ትከሻ ፡ ላይ ፡ ሆኜ (፪x) ተራሮች ፡ ቢወርዱ ፡ ወደባሕር ፡ ልብ (፪x) የያዝኩት ፡ አንተን ፡ ነው ፡ የነፍሴ ፡ መልህቅ (፪x) የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የሕይወት ፡ መገኛ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛ (፪x) መታመኛ ፡ መመኪያዬ ፡ እኔ ፡ አለኝ ፡ የምለው ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ የእኔ ፡ ጋሻ ፡ ማምለጫዬ ፡ የዘለዓለም ፡ ክብሬ ፡ ሆነኝ ፡ አለኝታዬ መመኪያዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ (፬x) የድል ፡ መሰረቴ ፡ መደላደላዬ (፪x) እንድኖር ፡ ያደረከኝ ፡ በአንተ ፡ እፎይ ፡ ብዬ (፪x) ጀርባ ፡ አልሰጠኸኝም ፡ በጠላቴ ፡ ፊት ፤ በሚጠላኝ ፡ ጊት ይልቁን ፡ ቀባኸኝ ፡ ራሴን ፡ በዘይት (፪x) ነፍሴን ፡ በከበረው ፡ ሰረገላ ፡ አስቀምጠህ ፡ ሞላኸኝ ፡ በምሥጋና የእኔ ፡ ጌታ ፡ እንደአንተማ ፡ ለእኔ ፡ ማንም ፡ የለም ሾሜሃለሁ ፡ ግዛ ፡ በሕይወቴ ፡ ለዘለዓለም ኢየሱሴ ፡ እንደ ፡ አንተማ ፡ ለእኒ ፡ ማንም ፡ የለም ሾሜሃለሁ ፡ ግዛ ፡ በሕይወቴ ፡ ለዘለዓለም መታመኛ ፡ መታመኛዬ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ (፬x) የታል ፡ የትናንቱ ፡ የከበደኝ ፡ ነገር (፪x) እንደጉም ፡ በነነ ፡ ከላይ ፡ ስትናገር (፪x) አዲስ ፡ የድል ፡ ምዕራፍ ፡ ተቀዳጅቻለሁ (፪x) በአንተ ፡ በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ ዘልያለሁ (፪x) የዘለዓለም ፡ አምላክ ፡ የሕይወት ፡ መገኛ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆንክልኝ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛ (፪x) መታመኛ ፡ መታመኛዬ ፡ ተባረክ ፡ ጌታዬ (፬x)