Loading
ያልሰጠኸኝ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ቀረብኝ ፡ የምለው እንዴት ፡ ይሄን ፡ ይጠይቅ ፡ ከሞት ፡ የታደከው ፍላጐቴ ፡ ሞላልኝ ፡ ምኞቴም ፡ ተሳካ የሁሉ ፡ መደምደሚያ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ለካ አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x) ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ስንፍና ፡ አላወራም ፡ ክፉ ፡ አይወጣም ፡ ከአፌ ሁሌ ፡ ያስደንቀኛል ፡ ከሞቴ ፡ መትረፌ ይሄ ፡ ቀረብኝ ፡ ብዬ ፡ አላማህም ፡ ለሰው ደም ፡ አፍሳሹን ፡ ክፉ ፡ ሰው ፡ ወደህ ፡ ከታደከው አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x) ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ቆም ፡ ብዬ ፡ ሳስበው ፡ የሆነከውን ፡ ለእኔ ለዘለዓለም ፡ ታደከኝ ፡ ከዚያ ፡ ከኩነኔ ቀራንዮ ፡ ይናገር ፡ ጐልጐታ ፡ ይመስክር ለመስቀል ፡ ሞት ፡ አበቃህ ፡ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር አዝ፦ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ ምሥጋና ፡ ልሰጥ መጣሁ ፡ ወደ ፡ ደጅህ ፡ አምልኮ ፡ ልሰጥ (፪x) ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌ ፡ ሃሌሉያ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.