Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም ፡ ነው በመከራ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ ነው አምላካችን ፡ መልካም ፡ ነው ፡ መልካም ፡ ነው በመከራ ፡ ቀን ፡ መሸሸጊያ ፡ ነው በመልካም ፡ መንገድ ፡ የሚመራ ፡ ያመኑትን ፡ የማያሳፍር ለተጨነቁት ፡ ፈጥኖ ፡ ደራሽ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ቃሉን ፡ የሚያከብር ዝናብ ፡ ደመና ፡ በሌለበት ፡ ምድረ ፡ በዳውን ፡ አለምልሞ በፍፁም ፡ በረከት ፡ ያኖራል ፡ በድንቅ ፡ ስራው ፡ አስገርሞ አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው (መልካም) (፬x) መሸሸጊያ ፡ ነው ፡ መሸሸጊያ ፡ መሸሸጊያ (፬x) እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) (፬x) ሁን ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ የሚሆንለት ፡ ሥሙ ፡ ገናና ፡ የከበረ ሃሳቡ ፡ የማይከለከል ፡ ያለ ፡ የሚኖር ፡ የነበረ አዋጅ ፡ ገልብጦ ፡ የሚያከብር ፡ ከእቶን ፡ እሳት ፡ የሚያድን መልካም ፡ እረኛ ፡ የት ፡ ይገኛል ፡ እንደ ፡ ክርስቶስ ፡ የሚሆን አዝ፦ መልካም ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር መልካም ፡ ነው (መልካም ፡ ነው) (፬x) እያየሁኝ ፡ ሲረዳኝ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁኝ እግዚአብሔር ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ እቀኛለሁ (፪x)