Loading
Singer
ተራራው ፡ ከፊቴ ፡ እንደሰም ፡ ቀለጠ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ ቃልህም ፡ ሲወጣ ፡ ጫካው ፡ ተገለጠ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ እግሮቼም ፡ ፀኑልኝ ፡ እንደዋላ ፡ እግር ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ ረዳት ፡ ሆነኸኛል ፡ አምላኬ ፡ ክበር ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ አዝ፦ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዕዋት (፪x) ሆነኸኝ ፡ አይቻለሁ ፡ አባት (፪x) ላክብርህ ፡ እኔ ፡ ደጋግሜ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ላዚም ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ (፪x) አቤቱ ፡ ተደንቄያለሁኝ ፡ እና (፪x) ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፬x) ምህረትህ ፡ ከሕይወት ፡ በርግጥም ፡ ይበልጣል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ ደጅ ፡ ጥናት ፡ የለም ፡ በፍጥነት ፡ ያነሳል ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ ድንጋይ ፡ ተደርድሮ ፡ ሞት ፡ ሲጠብቃት ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ ሀፍረቷን ፡ ሸፍነህ ፡ ሰላም ፡ ሂጂ ፡ አልካት ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ አዝ፦ ልሰዋ ፡ የምሥጋናን ፡ መስዕዋት (፪x) ሆነኸኝ ፡ አይቻለሁ ፡ አባት (፪x) ላክብርህ ፡ እኔ ፡ ደጋግሜ (፪x) ከፍ ፡ በል ፡ ላዚም ፡ ፊትህ ፡ ቆሜ (፪x) አቤቱ ፡ ተደንቄያለሁኝ ፡ እና (፪x) ልሰዋ ፡ ምሥጋና (፬x)