Loading
Singer
አዝ፦ ምሥጋናህ ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፬x) ላመሰግንህ ፡ እወዳለሁ (፫x) ላመሰግንህ ፡ እፈቅዳለሁ (፫x) ቀንበረን ፡ ከጫንቃዬ ፡ ላይ ፡ ሰበርከው ፡ አሃሃሃ የከበደኝን ፡ ሸክሜን ፡ አራገፍከው ባዶነቴን ፡ በፍቅርህ ፡ ሞላኸው ደስታዬን ፡ ከወይን ፡ ፍሬ ፡ ይልቅ ፡ አበዛኸው ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x) ምሥጋናህ ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፬x) ላመሰግንህ ፡ እወዳለሁ (፫x) ላመሰግንህ ፡ እፈቅዳለሁ (፫x) በሕይወት ፡ መዝገብህ ፡ ላይ ፡ ስሜን ፡ ጻፍከው ኑሮዬን ፡ ታሪኬን ፡ በሙሉ ፡ ለወጥከው በደስታ ፡ ዘይት ፡ ራሴን ፡ ስትቀባ ሰላምን ፡ ኢኸው ፡ በቤቴ ፡ ውስጥ ፡ ገባ ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x) ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x) ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x) ሊቋቋሙን ፡ ከቶ ፡ አልቻሉም ፡ ጠላቶቼ በስምህ ፡ አሸነፍኳቸው ፡ ተዋግቼ እግሬን ፡ በአንገታቸው ፡ ላይ ፡ አኑሬያለሁ በደስታ ፡ የድል ፡ ዝማሬን ፡ ዘምራለሁ መክበቡን ፡ ዙሪያዬን ፡ ከቦኝ ፡ ነበረ ያሰብክልኝ ፡ ስፍራ ፡ እንዳልደርስ ፡ ብዙ ፡ ጣረ አንተ ፡ ግን ፡ ሁሉን ፡ ጥሰህ ፡ አሳለፍከኝ ጠላቴ ፡ ዓይኑ ፡ እያየ ፡ ከፍ ፡ አረከኝ ታዲያ ፡ ምን ፡ ልክፈልህ ታዲያ ፡ ምኔን ፡ ልስጥህ እንዲሁ ፡ አንተን ፡ ልባርክህ (፪x) ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x) ተመስገን ፡ ለዘላለም ፡ ተመስገን (፪x)