Loading
Singer
<poem> ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ ይዤ ፡ መጣሁ አንተን ፡ የሚመስል ፡ አጣሁ ተወደስ ፡ ተቀደስ ፡ ለዘለዓለም የሚወዳደር ፡ የለም ፡ (አንተን ፡ የሚመስል ፡ የለም) (፬x) የፀሐይ ፡ ድምቀትዋ ፡ የምድር ፡ ስፋቷ የውቂያኖስ ፡ ጥልቀት ፡ የሰማይ ፡ ርቀት አንተ ፡ ባለግርማ ፡ ከማን ፡ ላወዳድርህ ወጥቸ ፡ ወርጀ ፡ አጣሁ ፡ የሚመስልህ ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x) የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ ምሥጋና ፡ አምልኮ የነፋስ ፡ ሽውታ ፡ የእጽዋት ፡ ሽታ የወንዝ ፡ የጅረቱ ፡ የአእዋፍ ፡ የአራዊቱ አድንቄ ፡አድንቄ ፡ ሁሉን ፡ በየተራ መጨረስ ፡ አልቻልኩም ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ስራ ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x) የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ ምሥጋና ፡ አምልኮ የሰው ፡ ልጆች ፡ ውበት ፡የጀግኖቹ ፡ ጉልበት የባለጸጋው ፡ ፍርድ ፡ የጠቢባን ፡ ጥበብ ከማን ፡ ላወዳድረው ፡ ጌታ ፡ የአንተን ፡ ዝና በዘመናት ፡ ሁሉ ፡ ብቻህን ፡ ገናና ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x) የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው አዝ ምሥጋን ፡ አምልኮ ቅኔው ፡ ማህሌቱ ፡ የሙዚቃው ፡ ስልቱ ስዕሉም ፡ ተኩሎ ፡ ማን ፡ አንተን ፡ አክሎ ቃላት ፡ አይገልጹህም ፡ ታላቅነትህን በገባን ፡ መጠን ፡ እናክብር ፡ ስምህን ክረምት ፡ አለፈ ፡ በጋው ፡ መጣ አንዱ ፡ ወረደ ፡ ሌላው ፡ ወጣ ግን ፡ እስከዛሬ ፡ ሕያው ፡ የሆነው የእኛው፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው (አማኑኤል ፡ ብቻ ፡ ነው) (፪x) የእኛ፡ ጌታ ፡ ብቻ ፡ ነው የእኛ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው