Loading
Singer
ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው (፪x) ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x) እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) ሠማያዊ ፡ ብርሃን ፡ በልቤ ፡ ውስጤ ፡ በርቷል የጌታዬ ፡ ማዳን ፡ ነፍሴን ፡ አግኝቷታል ከዘለዓለም ፡ ጥፋት ፡ ከፍርድ ፡ አምልጫለሁ በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ አዲስ ፡ ሰው ፡ ሆኛለሁ ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x) ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x) እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) ክቡር ፡ ኃያል ፡ ጌታ ፡ የእስራኤል ፡ ተዋጊ በአለቀ ፡ ሰዓት ፡ ላይ ፡ የምስደርስ ፡ ታዳጊ አዋጅን ፡ በአዋጅ ፡ በሥልጣንህ ፡ ሽረህ በድል ፡ አራመድከኝ ፡ ታሪኬን ፡ ቀይረህ ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x) ምሥጋና ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ዝማሬ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው አምልኮ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ውዳሴ ፡ ሲያንስህ ፡ ነው ከአደረከው ፡ ጋራ ፡ ሳወዳድረው ከሰራኸው ፡ ጋራ ፡ ሳመዛዝነው ከተደረገልኝ ፡ ነገር ፡ አንዱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር (፪x) እንዲሁ ፡ በፀጋ ፡ ወደህ ፡ ከአደረከው ጌታ ፡ ክበር ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) ፊትህ ፡ እቀርባለሁ ፡ በብዙ ፡ ምሥጋና ጌታ ፡ ለውለታህ ፡ ምላሽ ፡ የለኝምና የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ እንካ ፡ ተቀበለው ሕያው ፡ መስዕዋቴ ፡ ማደሪያህን ፡ ይሙላው ኢኸው ፡ ምሥጋናዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ ኢኸው ፡ ዝማሬዬን ፡ ለአንተ ፡ አበዛለሁ (፪x)