Loading
Singer
ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x) መከራ እንደሚያልፍ የጊዜውም ሃዘን እንደምንራመድ ሁሉን ነገር አልፈን ለቅሶ በዝማሬ ሃዘን በደስታ እንደሚለወጡ ተናግሯል ያ ጌታ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x) እንደበደላችን አልተከፈለንም ጌታ በመዓቱ አልተናኘንም ምህረትን የሚወድ የሰራዊት ጌታ እዳዬን ለመክፈል በውርደት ተመታ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪x) በኑሮዬ ሁሉ አንተን አስከብሬ በመከራ ልለፍ ከአንተ ጋር አብሬ የሕይወት እስትንፋስ ሰጥተኸኛልና መስዋዕቴ ይኸው ከነፍሴ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (፪)