Loading
Singer
ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ዝማሬ ፡ ለአንተ ፡ ዝማሬ ሙገሳ ፡ ሙገሳ ፡ ሙገሳ ፡ ለአንተ ፡ ሙገሳ ሰማየ ፡ ሰማያት ፡ ለአግዚአብሐር ፡ ምሥጋና በአርያምም ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና ሰራዊቱ ፡ ሁሉ ፡ ጌታን ፡ አመስግኑት ጽሀይና ፡ ጨረቃም ፡ እርሱን ፡ አመስግኑት ክዋክብትና ፡ ብርሃን ፡ እርሱን ፡ አመስግኑት የሰማያት ፡ በላይ ፡ ውሃም ፡ አመስግኑት እርሱ ፡ ብሏልና ፡ ሁኑ ፡ እነርሱም እርሱ ፡ አዞአልና ፡ ተፈጠሩም ሃሌሉያ ፡ እግዚአብሔር ፡ ይመስግን እግዚአብሔርን ፡ ከሰማይ ፡ አመስግኑት እግዜአብሔርን ፡ ከምድር ፡ አመስግኑት የእግዚአብሔርን ፡ ስሙን ፡ አመስግኑት የምድር ፡ ነገሥታት ፡ አህዛብም ፡ ሁሉ አለቆችና ፡ ፈራጆች ፡ ሁሉ ጐማሶችና ፡ ቆነጃጅቶች አመስግኑት ፡ ሽማግሌዎች ፡ ልጆች ሥሙ ፡ ብቻውን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሏል ፡ ምሥጋናው ፡ በሰማይ ፡ እና ፡ በምድር ፡ ሆኗል የሕዝቡንም ፡ ቀንድ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል ለእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ ምሥጋና ፡ ይገባል