Loading
Singer
ፈረሱንና ፡ ፈረሰኛውን በባሕር ፡ የጣለ ፡ እኛን ፡ አሻግሮን በሚያስፈራ ፡ ግርማው ፡ ከፊት ፡ እየመራ ነጥቆ ፡ ያስመለጠን ፡ ከዚያ ፡ ባለጋራ (፪x) አዝ፦ ትላንት ፡ የረዳን ፡ ያገዘን ፡ ጌታ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ አለና ፡ እንጨምር ፡ ምሥጋና (፪x) ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x) ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ ቀኑን ፡ በደመና እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ ለአፍታ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጥሎ ፡ የማይጠፋ የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ አለው ፡ ጽኑ ፡ ፍቅር ፡ ቀን ፡ ቢከፋ እንደኃያልና ፡ እንደጨካኝ ፡ ወጥቶ በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ ላይ ፡ ውጊያውን ፡ ተዋግቶ ድል ፡ አድርጐ ፡ ባለድል ፡ ያደረገን ፡ እርሱ ፡ ነው ይክበር ፡ ይንገሥልን ፡ ወደን ፡ እናምልከው ፡ ፈቅደን ፡ እናምልከው አዝ፦ ትላንት ፡ የረዳን ፡ ያገዘን ፡ ጌታ ዛሬም ፡ በዙፋኑ ፡ አለና ፡ እንጨምር ፡ ምሥጋና (፪x) ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x) ሌሊት ፡ በእሳት ፡ አምድ ፡ ቀኑን ፡ በደመና እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ ለአፍታ ፡ ደክሞ ፡ አያውቅም መንገድ ፡ አስጀምሮ ፡ ጥሎ ፡ የማይጠፋ የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ አለው ፡ ጽኑ ፡ ፍቅር ፡ ቀን ፡ ቢከፋ ብዙ ፡ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (፪x)