Loading
Singer
ሃሌሉያ : ሃሌሉያ : ሃሌሉያ አሳዳጃችን ፡ ከባሕር ፡ ሰጥሞ ምድረ ፡ በዳችን ፡ በአንተ ፡ ለምልሞ ከያለንበት ፡ ተሰብስበናል እኛም ፡ ሰው ፡ ሆነን ፡ ሰውን ፡ ማርከናል አዝ፡- ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ በሰው ፡ ልጅ ፡ኀጢአት ፡ ምድርን ፡ብትቀጣ የመከራ ፡ ጐርፍ ፡ ከላይ ፡ ቢመጣ በዙሪያችን ፡ አጥር ፡ ሰርተሃል ለእኛ ፡ ለሕዝብህ ፡ መርከብ ፡ ሆነሃል አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ የፈርኦን ፡ ጦር ፡ ሕዝቡን ፡ አሳዶ እርሱ ፡ ግን ፡ ቀረ ፡ ከባሕር ፡ ማዶ እርስታችንን ፡ በድል ፡ ወርሰናል በአንተ ፡ እረኝነት ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል አዝ፦ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ፡ ምሥጋና ከአእምሮያችን ፡ በላይ ፡ ለሆነው ፡ ውለታህ ቆጥረን ፡ እስከማንዘልቅ ፡ ለበዛው ፡ ስጦታህ እናከብርሃለን ፡ ክበርልን ፡ ጌታ