Loading
Singer
አዝ፦ ስራዬን ፡ ሰርተህልኛል ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህልኛል መንገዴ ፡ ተቃንቶልኛል ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ሆኖልኛል በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x) አንተ ፡ የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ውዴ ፡ የሰላሜ ፡ ንጉሥ ከትቢያ ፡ ላይ ፡ ያነሳኸኝ ፡ ክበር ፡ ተመስገን ፡ ኢየሱስ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ሁሉ ፡ አይቻለሁ ፡ ማዳንህን ሳልታክት ፡ አወራዋለሁ ፡ አምላኬ ፡ ሕያው ፡ ስራህን በተከበበ ፡ ከተማ ፡ ምህረትህ ፡ በዝቶልኝ በድል ፡ መንገድ ፡ እየመራህ ፡ ከጠላቴ ፡ አስጥለኀኝ የሞተውን ፡ ማንነቴን ፡ ሕይወት ፡ ዘርተህበታል ከብረህልኛል ፡ በቤቴ ፡ በረከትህ ፡ በርክቷል (፪x) አዝ፦ ስራዬን ፡ ሰርተህልኛል ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህልኛል መንገዴ ፡ ተቃንቶልኛል ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ሆኖልኛል በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x) የዓለም ፡ እንከን ፡ የሞላበት ፡ ውል ፡ አልባ ፡ ሆኖ ፡ መንገዴ አንተን ፡ እንዳላይ ፡ ከልሎኝ ፡ አጉል ፡ ወግና ፡ ልማዴ ምንም ፡ በጐነት ፡ ሳይኖረኝ ፡ እንዲያው ፡ ምህረት ፡ አግኝቼ የደምህ ፡ ፍሬ ፡ ሆኛለሁ ፡ ከኀጢአት ፡ ባሕር ፡ ወጥቼ ምሥጋናዬን ፡ ልሰዋልህ ፡ ክበርልኝ ፡ ዘለዓለም በዘመኔ ፡ ሁሉ ፡ ለእኔ ፡ እንዳንተ ፡ መልካም ፡ የለም እፎይ ፡ ብያለሁ ፡ አርፌ ፡ ሆነኸኛል ፡ ሰላሜ ተባረክልኝ ፡ ልበልህ ፡ ደግሜ ፡ ደጋግሜ (፪x) አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x) የሞተውን ፡ ማንነት ፡ ሕይወትን ፡ ዘርተህበት ጽድቅህን ፡ ሰጥተኸኝ ፡ ለእኔ ፡ ነፃ ፡ አረግከኝ ፡ ከኩነኔ አዝ፦ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ፡ ወድደኸኛልና ምሥጋና ፡ አይጠፋም ፡ ከአፌ ፡ ምሥጋና (፬x)