Loading
Singer
አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x) አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ ተረስቻለሁ ፡ ጌታ ፡ ትቶኛል የተጣልኩኝ ፡ ነኝ ፡ ማን ፡ ያስበኛል ብዬ ፡ ሳነባ ፡ የራራህልኝ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ስላስታወስከኝ አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x) አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ ቤት ፡ የሌለው ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ ከርታታ ያደላደልከኝ ፡ የእረፍቴ ፡ ጌታ ለልቤ ፡ ትምክህት ፡ ስለሆንክልኝ ከፍ ፡ በል ፡ ውዱ ፡ አምላኬ ፡ ስላከበርከኝ አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x) አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ ባዶ ፡ ሕይወቴን ፡ በዘይት ፡ ሞልተህ የነፍሴን ፡ ጥማት ፡ ከእጅህ ፡ አርክተህ በፍቅርህ ፡ ስበህ ፡ ሰው ፡ ስላረከኝ ተባረክ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ስለባረከኝ አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x) አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ አንተ ፡ ጌታዬ ፡ ሁሌ ፡ በምክርህ ሰው ፡ እንዳይጠፋ ፡ ነውና ፡ ሃሳብህ በሕይወት ፡ ቃልህ ፡ ልቤን ፡ አፀናህ ከፍ ፡ በል ፡ በምድር ፡ ይግነን ፡ ክብርህና ፡ ዝናህ አዝ፦ ምሥጋና ፡ ተሞልታለች ፡ ነፍሴ (፪x) አቀርብልሃለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ ቸርነትህ ፡ ብዙ ፡ ውዱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ አጐናጽፈኸኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ደስታ