Loading
Singer
አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም በሰማይ ፡ ተቀምጠህ ፡ ከፍ ፡ ባለ ፡ ስፍራ በምድር ፡ ሆኜ ፡ ትንሽ ፡ ሰው ፡ እርዳኝ ፡ ብዬ ፡ ስጣራ ሰምተህ ፡ ከመለስከኝ ፡ ቀኝህ ፡ ከረዳችኝ ላመስግን ፡ በዘመኔ ፡ ክንድህ ፡ ካገዘችኝ ኦሆ ፡ ክንድህ ፡ ካገዘችኝ አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም ዮርዳኖስ ፡ ሲከፈል ፡ ተዓምር ፡ ማሳያ ከመሃል ፡ ድንጋይ ፡ ወጣ ፡ ሆነ ፡ መታሰቢያ እኔም ፡ በዚህ ፡ ዘመን ፡ ሥራህን ፡ ስላየሁ ሕያው ፡ ለመሆንህ ፡ ምስክር ፡ እሆናለሁ ኦሆ ፡ ምስክር ፡ እሆናለሁ እንኳን ፡ ወዳጆቼ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ እኔም ፡ ለእራሴ አስቤው ፡ አላውቅም ፡ በህልሜም ፡ በውኔ (፪x) ጠላቶቼማ ፡ የኔን ፡ ውድቀት ፡ የሚሹ አሳፈርካቸዉ ፡ ታምራትህን ፡ አዩ (፪x) በለቅሶ ፡ ተዘርቶ ፡ በደስታ ፡ ከታጨደ በኩርንችት ፡ ፈንታ ፡ ባርሰነት ፡ ከበቀለ ንጉሥ ፡ ለሚወደው ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ይደረጋል ማይጠፋ ፡ ምልክት ፡ ነው ፡ ዓይኔ ፡ ይህን ፡ አይቷል ኦሆ ፡ ዓይኔ ፡ ይህን ፡ አይቷል አዝ፦ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ አምላክ ፡ እንደሆንክ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ ጌታ ፡ እንደሆንክ እመሰክራለሁ ፡ እንደምትረዳ ምስክር ፡ ነኝ ፡ እኔ ፡ እንደምትደርስ ፡ ለተጐዳ እኔን ፡ ያዩ ፡ ዓይኖችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ የሰሙ ፡ ጆሮዋችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያነሱ ፡ እጆችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እኔን ፡ ያጽናኑ ፡ ቃሎችህ ፡ ይባረኩ ፡ ለዘላለም እንኳን ፡ ወዳጆቼ ፡ እዚህ ፡ መድረሴ ፡ እኔም ፡ ለእራሴ አስቤው ፡ አላውቅም ፡ በህልሜም ፡ በውኔ (፪x) ጠላቶቼማ ፡ የኔን ፡ ውድቀት ፡ የሚሹ አሳፈርካቸዉ ፡ ታምራትህን ፡ አዩ (፪x)