Loading
Singer
Updated 3d ago
ምሳሌዬ ፡ አንተው ፡ ነህ ፡ በምግባርህ ፡ የማውቅህ ንግግርህ ፡ ከሩቅ ፡ ይጠራል ፡ ጨዋነትን ፡ ተላብሰሃል ከውስጤ ፡ ገብተህ ፡ ቀርተሃል ፡ ማን ፡ ቢፈለግ ፡ ይተካሃል ጥበብ ፡ ፍቅርም ፡ በአንተ ፡ ይለካል ፡ አዋቂነትስ ፡ ከአንተ ፡ ይቀዳል አዝ:- አስተዋይ ፡ ወዳጄ ፡ ብልህ ፡ ብትገባኝ ፡ ነው ፡ ባውቅህ ጠቢብ ፡ ብዬ ፡ ብጠራህ ፡ ቃል አጥቼ ፡ ለስምህ ጻድቅ ፡ ፍፁም ፡ ነህ (፬x) አለቅነት ፡ በአንተ ፡ ያምራል ፡ አስተዳደር ፡ በአንተ ፡ ይሰላል መታገስህ ፡ ሁሉን ፡ ያልፋል ፡ መቼ ፡ ፍርድህ ፡ ቀድሞ ፡ ያውቃል የሊቅ ፡ ጥጉ ፡ መደምደሚያ ፡ የትሁት ፡ ልብ ፡ ማሳረጊያ ፍትህ ፡ ሚዛኑ ፡ በአንተ ፡ ከወጣ ፡ ዳኝነቱም ፡ ካንተ ፡ ይምጣ አዝ:- አስተዋይ ፡ ወዳጄ ፡ ብልህ ፡ ብትገባኝ ፡ ነው ፡ ባውቅህ ጠቢብ ፡ ብዬ ፡ ብጠራህ ፡ ቃል አጥቼ ፡ ለስምህ ጻድቅ ፡ ፍፁም ፡ ነህ (፬x) የሁሉን ፡ ከፍታ ፡ ይዘሃል ፡ ወርደህም ፡ አዳምን ፡ ሁነኃል ከፍም ፡ ብለህ ፡ ዝቅም ፡ ብለህ ፡ ፍፁም ፡ ጌታ ፡ አንድ ፡ አንተ ፡ ነህ ሁሉን ፡ በእኩል ፡ የምታየው ፡ ምስኪኑንም ፡ የማትንቀው የደግነት ፡ መገለጫ ፡ የሁሉ ፡ አባት ፡ አንተ ፡ ብቻ ውዴ ፡ ውበትህ ፡ ማንነትህ ፡ ደም ፡ ግባትህን አይቼው ፡ አይቼው ፡ አልችልም ፡ ልገልጽህ (፬x)