Loading
Singer
የቆምኩበት ፡ ስፍራ ፡ ይህ ፡ ግዑዙ ፡ መሬት ፡ ግዑዙ ፡ መሬት የሰላም ፡ ነው ፡ የደም ፡ ጠብ ፡ የበቀለበት ፡ ጠብ ፡ የበቀለበት የእርምጃዬ ፡ ማብቂያ ፡ የእግሮቸን ፡ አቅጣጫ ፡ የእግሮቸን ፡ አቅጣጫ መርምር ፡ ሩጫዬን ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ፡ የሕይወቴን ፡ ምርጫ ልቤን ፡ ብትከፍተው ፡ ጫካኝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ገራም ፡ ጫካኝ ፡ ነው ፡ ወይ ፡ ገራም የእጆቸ ፡ መዘርጋት ፡ ለሰይፍ ፡ ነው ፡ ለሰላም ፡ ለሰይፍ ፡ ነው ፡ ለሰላም ሌሊት ፡ በምንጣፌ ፡ በጭርታው ፡ ሰዓት ፡ በጭርታው ፡ ሰዓት የማውጠነጥነው ፡ የአዕምሮዬ ፡ ሙላት ፡ የአዕምሮዬ ፡ ሙላት የአዕምሮዬ ፡ ሙላት የአዕምሮዬ ፡ ሙላት ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል ፍጥረት ፡ እርቃኑን ፡ ነው ፡ ግልጥልጥ ፡ ብሏል ድልድል ፡ ቢሆን ፡ወይ ገደላማ በራ ፡ ቢሆን፡ ወይ ፡ ደመናማ እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ ደረቅ ፡ መሬት ቢሆን፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ የሚያልፍህ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል ዓይኖቼ ፡ ተከፍተው ፡ ወዴት ፡ አማተሩ ፡ ወዴት ፡ አማተሩ የምላሴ ፡ ቅምሻ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ መራሩ ፡ ጣፋጭ ፡ ነው ፡ መራሩ ቃሌ ፡ የአንደበቴ ፡ የሚወረወረው ፡ የሚወረወረው ለጐረቤት ፡ ጆሮ ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው ፡ በራድ ፡ ወይ ፡ እሳት ፡ ነው የፊቴ ፡ ገታ ፡ ውጫዊ ፡ ምስሌ ፡ ውጫዊ ፡ ምስሌ ላየኝ ፡ በሩቅ ፡ መሳይ ፡ ሁሉን ፡ መደለሌ ፡ ሁሉን ፡ መደለሌ ከብላቴንነት ፡ ከቶ ፡ መች ፡ ጠቀመኝ ፡ ከቶ ፡ መች ፡ ጠቀመኝ ውስጤን ፡ የምታይ ፡ ሆይ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ መርምረኝ ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል ፍጥረት ፡ እርቃኑን ፡ ነው ፡ ግልጥልጥ ፡ ብሏል ድልድል ፡ ቢሆን ፡ ገደላማ ብራ ፡ ቡሆን ፡ ወይ ፡ ደመናማ እዚህ ፡ በቅርብ ፡ ወይ ፡ እዚያ ፡ በሩቅ ደረቅ ፡ መሬት ፡ ወይ ፡ ውኃ ጥልቅ በምድር ፡ በታች ፡ በአየር ፡ በላይ የሚያልፍ ፡ የለም ፡ ዓይንህ ፡ ሳያይ ከአንተ ፡ (፫ጊዜ) ምን ፡ የደበቃል