Loading
Singer
መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ ዛሬ ላንተ ቆሜ ባፌ ዘምራለሁ ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህ አንተን ያገኘሁ ለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያፀድቃል (2) ስንከራተት ሳለ በምድረበዳ ላይ የሚረዳኝ የለም ግራ ቀኜን አላይ ባልጠበኩት ለታ ከሰማይ ድምፅ መጣ በእጁ እጄን ያዘኝ ተራራን አወጣኝ አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ በእውነት ቃል አስቤህ ለክብር ወልጄሃለሁ ለዘላለም ፍቅሬ ካንተ አትለይም አለኝ ለዘለዓለም እኔ አልጥልህም አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ) እርጥበት የማያውቅ በድርቅ የደቀቀ ህይወቴ ነበረ ከአጥንት የደረቀ ከፍጥረቴ ሳለሁ የበረሃ ወይራ መጠጊያን አገኘሁ በመልካሙ ስፍራ ኩሩው ሊያስቀና ምስኪኑን መረጠ ከውድረደት አንስቶ ለክብር አስቀመጠ በእርሱ ተተክዬ በመልካሙ ግንድ ስር ልምላሜን አገኘሁ ለዘላለም ይክበር አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ) ጠመዝማዛ ጉዞ ቁልቁለት ሳዘግም ሞቴን ለማፋጠን ኃጥያትን ስቃርም በጠላት ድለላ በእርሱ ጦር ታጅቤ ከፍቅር አባቴ ካንተ ሲሸሽ ልቤ እንደ ህጻን አርገህ በእርጋታ መከርከኝ ሳላውቅ እንዳልጠፋ ፍቅርህ ሰበሰበኝ አንተ ካስጠጋኸኝ የሚከሰኝ ማነው ነፃ ያወጠኸኝ ከልብህ ወደህ ነው አንተን ያገኘሁ ለት (አዝ)