Loading
Singer
መኖሪያዬ ፡ የዘላለም ፡ አምላክ ፡ ነው በክንዶቹ ፡ ጥላ ፡ አርፋለሁ የሚያስፈራኝ ፡ ሁሉ ፡ ተወግዷል ህይወቴን ፡ በሰላም ፡ ሞልቶታል (፪x) አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የለም ፡ የሚመስለው ፡ እግዚአብሔር ፡ እጅግ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ (፪x) እንዲህ ፡ ነህ ፡ ተብሎ ፡ ማይገመተው ከሰው ፡ ልጅ ፡ እጅግ ፡ የላቀ ፡ ከፍም ፡ ያለ ፡ ነው አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም ፡ አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x) የሞተውን ፡ ነገር ፡ ህያው ፡ ነው ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው ያለቀውን ፡ ነገር ፡ ይሞላል ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው (፪x) እረኛውን ፡ አይቶ ፡ ንጉስ ፡ ነህ ፡ የሚለው ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ነው/2 አዝ፡ ፡ የለም ፡ እንደ ፡ ጌታ ፡ የለም የለም ፡ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ የለም አይኖርም ፡ ዘላለም (፪x)