Loading
Singer
መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ መንገድ ፡ አለው ባሕርን ፡ የሚከፍል ፡ ንፋስን ፡ ያመጣል ውሃውን ፡ አስወግዶ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል ኃይለኛውንም ፡ ወንዝ ፡ እርሱ ፡ ያቆመዋል ደርቅ ፡ መንግድ ፡ አድርጐ ፡ ማሻገር ፡ ይችላል ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም ተራራውን ፡ አዞ ፡ ይደለድለዋል ሸለቆውን ፡ ከፍ ፡ አድርጐ ፡ መንገድ ፡ ያደርገዋል የእግዚአብሔር ፡ መንገድ ፡ በቀን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ሌሊቱም ፡ በእርሱ ፡ ዘንድ ፡ ጨለማ ፡ አይሆንም ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም ደመናም ፡ ባይታይ ፡ ነፍሱም ፡ ባይነፍስም ለመጽናናት ፡ የሚሆን ፡ ምልክት ፡ ባይኖርም መንገድ ፡ አለው ፡ ጌታ ፡ ውሃውን ፡ ያመጣል የሌለውን ፡ ጠርቶ ፡ ማኖር ፡ ያውቅበታል ፡ በእግዚአብሔር ፡ ተስፋ ፡ አይቆረጥም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ የሚሳነው ፡ የለም