Loading
Singer
አዝ፦ መንፈስህን ፡ አትውሰድብኝ አብሮነትህ ፡ ከእኔ ፡ አይለይ ፡ እኔ??? መገኘትህ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሰላሜ ሃብቴ ፡ ቅርሴ ፡ እስከዘለዓለሜ ፈቃድህን ፡ ሃሳብህን ፡ ትቼ ስቅበዘበዝ ፡ ከቤትህ ፡ ጠፍቼ ፈቃድህን ፡ መንገድህን ፡ ትቼ ስቅበዘበዝ ፡ ከቤትህ ፡ ጠፍቼ ክብር ፡ ጠፍቶ ፡ ቅጥር ፡ ፈርሶ ጠላት ፡ ገባ ፡ ወደቤቴ ሰላም ፡ ቀርቶ ፡ ለቅሶ ፡ ሞልቶት ዐይኔን ፡ በዕምባ እንዳልሸሽህ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ የልጅ ፡ ወጉ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ አባትዬ ፡ እልሃለሁ ድረስልኝ ፡ ጠፍቻለሁ ክብር ፡ ጠፍቶ ፡ ቅጥር ፡ ፈርሶ ጠላት ፡ ገባ ፡ ወደቤቴ ሰላም ፡ ቀርቶ ፡ ለቅሶ ፡ ሞልቶ ዐይኔን ፡ በዕምባ እንዳልርቅህ ፡ ትዝ ፡ እያለኝ የልጅ ፡ ወጉ ፡ ግድ ፡ ቢለኝ አባብዬ ፡ እልሃለሁ ድረስልኝ ፡ ጠፍቻለሁ አዝ፦ መንፈስህን ፡ አትውሰድብኝ አብሮነትህ ፡ ከእኔ ፡ አይለይ ፡ እኔ??? መገኘትህ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ሰላሜ ሃብቴ ፡ ቅርሴ ፡ እስከዘለዓለሜ ያለአንተማ ፡ አቅም ፡ የለኝ ፡ እኔ እግዚአብሔር ፡ ሃይሌ ፡ ነህ ፡ መድህኔ ያለአንተማ ፡ ጉልበት ፡ የለኝ ፡ እኔ እግዚአብሔር ፡ ሃይሌ ፡ ነህ ፡ መድህኔ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ አሳዘንኩህ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ (፪x) ብዙ ፡ ጊዜ ፡ በደል ፡ ሰራሁ ፡ ብዙ ፡ ጊዜ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ይቅር ፡ አልከኝ ብዙ ፡ ጊዜ ፡ ራርተህ ዛሬም ፡ ቆሜ ፡ ዘምራለሁ ስላቀፍከኝ ፡ በፍቅርህ (፪x)