Loading
Singer
መንፈስህን ፡ ከእኔ ፡ አትውሰድብኝ (፬x) ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝ እንደ ፡ አንተ ፡ ሚሆንልኝ ፡ ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ሌላ ሌላ ፡ ወዳጅ ፡ የለኝ ፡ እንደ ፡ አንተ ፡ ሚሆንልኝ የውስጡ ፡ ቆሽሾ ፡ ውጪውን ፡ አጥርቼ ትንኝ ፡ ያጠራው ፡ ግመል ፡ ያክል ፡ ውጬ ለሰው ፡ ታይታ ፡ ሚኖር ፡ ፈሪሳዊ ፡ ሆኜ ማለፍን ፡ አልሻም ፡ ከክብርህ ፡ ጐድዬ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ በፊትህ ፡ ራሴን ፡ ላሳይ አግዘኝ ፡ እጠራሃለሁ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አውቅሃለው (፪x) አትተወኝ ፡ አትጣለኝ ያላንተማ ፡ ሕይወት ፡ የለኝ (፬x) እንደልቤ ፡ ሳይሆን ፡ ልሁን ፡ እንደልብህ ልወረስ ፡ በክብርህ ፡ እጄን ፡ ይያዝ ፡ እጅህ መንፈስህ ፡ መሪዬ ፡ ይሁን ፡ እረኛዬ በእቅፍህ ፡ ውስጥ ፡ ነው ፡ ክብሬም ፡ ዋስትናዬ አቤቱ ፡ አምላኬ ፡ ሆይ በፊትህ ፡ ራሴን ፡ ላሳይ አግዘኝ ፡ እጠራሃለሁ ቸር ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ አውቅሃለው (፪x) መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሕይወቴ ፡ ትርጉም ፡ ነህ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የልቤ ፡ ማረፊያ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ሌላ ፡ አልመኝም መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አጽናኝ ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ አትተወኝ ፡ አትጣለኝ ያላንተማ ፡ ሕይወት ፡ የለኝ (፬x)