Loading
Singer
መንፈስ ፡ቅዱስ ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለዉ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚያኮራ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አለ መንፈስ ፡ቅዱስ ፡ በውስጤ ፡ ያለዉ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ ሚያስመካ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ሌላ ፡ ምን ፡ አለ ፡ (፬) ሌላ ፡ ማን ፡ አለ ፡ (፬) በኃይሌ ፡ አይደለም ፡ ወይም ፡ በብርታቴ ፡ መውጣቴ ፡ መግባቴ ፡ ያማረው ፡ ሕይወቴ በመንፈሱ ፡ እንጂ ፡ ሁሉን ፡ በሚችለው ደካማውን ፡ ብርቱ ፡ ብርቱ ፡ በሚያደርገው አለኝ ፡ እውነቱን ፡ ሚያስተምረኝ አለኝ ፡ መልካሙን ፡ ሚያሳየኝ በለመለመ ፡ መስክ ፡ የሚያሳድረኝ በረፍትም ፡ ዉሃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ሚመራኝ ፡ ያጽናናኛል ፡ ይደግፈኛል ፡ በጐነቱን ፡ ይገልጥልኛል መካሪዬ ፡ ነው ፡ አለኝታዬ ፡ ዘልቆ ፡ ሚኖር ፡ ውስጤ ፡ ጟዳዬ አለኝ ፡ እውነቱን ፡ ሚያስተምረኝ አለኝ ፡ መልካሙን ፡ ሚያሳየኝ በለመለመ ፡ መስክ ፡ የሚያሳድረኝ በረፍትም ፡ ዉሃ ፡ ዘንድ ፡ ሁሌ ፡ ሚመራኝ በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እመካለሁ በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እኮራለሁ በቅዱሱ ፡ መንፈስህ ፡ እጽናናለሁ ከቅዱሱም ፡ መንፈስህም ፡ እማራለሁ እኮራለሁ ፡ (፬) እመካለሁ ፡ (፬)