Loading
አለህ ፡ በውስጤ ፡ ሰላምህ ፡ በዝቶልኛል አለህ ፡ በላዬ ፡ ድል ፡ ማድረግ ፡ ሆኖልኛል አለህ ፡ ከጎኔ ፡ ስትረዳኝ ፡ አየሁህ አለህ ፡ በቤቴ ፡ ህይወቴን ፡ አጣፈጥህ (፪x) አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መጽናኛዬ አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ አቅም ሀይሌ ፡ ጓደኛዬ አንድ ፡ የሆነ ፡ ጉዳይ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ እስክትጨርስ ፡ ድረስ አይደለም ፡ ለጊዜ ፡ ወደ ፡ አብ ፡ እስከምትመለስ ሁሌም ፡ ክእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ ሆነሃል ፡ ወዳጄ በውስጤ ፡ በላዬ ፡ ከጎኔ ፡ ከደጄ (፪x) አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መጽናኛዬ አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ መበርቻዬ ፡ ጓደኛዬ እውርነት ፡ ቀርቶ ፡ ማየት ፡ ጀምሬያለሁ የልቦናዬን ፡ አይኖች ፡ በአንተን ፡ አግኝቻለሁ ድፍርሱን ፡ ህይወቴን ፡ በምክርህ ፡ አጥርተሃል ያላንተ ፡ እንደማልኖር ፡ ልቤ ፡ ይህን ፡ አውቋል (፪x) አዝ፦ መንፈስ ፡ ቅዱሰ ፡ መበርቻዬ አቅሜ ፡ ነህ ፡ ጉልበት ፡ ሃይሌ አማላጄ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ አቅሜ ፡ ኃይሌ ፡ ጓደኛዬ መጽናኛዬ ፡ ጓደኛዬ አለኝታዬ ፡ ጓደኛዬ መበርቻዬ ፡ መጽናኛዬ አለኝታዬ ፡ ጕደኛዬ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.