Loading
Singer
ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ፡ ታሪኬም ፡ አንተ ፡ ነህ ምንም ፡ ዝና ፡ የለኝ ፡ ዝናዬም ፡ አንተ ፡ ነህ ምንም ፡ ክብር ፡ የለኝ ፡ ክብሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ነህ ክብሬም ፡ ኢየሱስ ፡ ነህ (፪x) ታሪክን ፡ ለዋጭ ፡ ነህ ፡ ቀንበርን ፡ ሰባሪ እስራትን ፡ ፈቺ ፡ ደግሞም ፡ ድል ፡ አድራጊ ኧረ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ከወዴት ፡ ይገኛል ሠማይ ፡ በምድር ፡ ብዞር ፡ የት ፡ ይመጣል በመስቀል ፡ ላይ ፡ ለእኔ ፡ ራስህን ፡ ሰውተህ ለበደል ፡ ለኃጥያቴ ፡ አንተ ፡ ቆስለህልኝ ተውጬ ፡ እያለሁ ፡ በድቅድቅ ፡ ጨለማ ሞትን ፡ ሞተህልኝ ፡ ብርሃን ፡ ለእኔ ፡ አበራ