Loading
Singer
አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ (፪x) እኔም ፡ እንደሌላው ፡ አለሁኝ ፡ ነበርኩኝ ፡ ብዬ ፡ ምናገረው ከበደሌ ፡ ሌላ ፡ ምንም ፡ ነገር ፡ የለኝ ፡ የምዘረዝረው ሰው ፡ መስሎት ፡ ቢክበኝ ፡ ሁሉን ፡ እንደከንቱ ፡ ቆጥሬ ፡ እተዋለሁ ይልቁን ፡ በሞቱ ፡ ጌታን ፡ እንድመስለው ፡ ለዚያ ፡ እዘረጋለሁ አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ ከመቃብር ፡ ወዲህ ፡ ቀሪ ፡ የሆነውን ፡ ታሪክ ፡ ከምሰራ ጊዜ ፡ የሚሽረውን ፡ ነገ ፡ የሚረሳውን ፡ ዝና ፡ ከማወራ ዘላለማዊውን ፡ ሕይወት ፡ የሆነውን ፡ ላውዛ ፡ ያንን ፡ ዜና የእግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ፍቅር ፡ የጌታችን ፡ ታሪክ ፡ እርሱ ፡ ይበልጣልና አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ ከአምላክ ፡ ጥሪ ፡ ሰምተው ፡ ለአምላካቸው ፡ ወንጌል ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ የሚለፉ በዚያ ፡ በማይጠፋው ፡ በሕይወት ፡ መጽሃፍ ፡ ላይ ፡ ተግተው ፡ የሚጽፉ በበጉ ፡ ዙፋን ፡ ፊት ፡ በጻድቃን ፡ ማህበር ፡ ስማቸው ፡ ሲጠራ በነፍስ ፡ ተወራርደው ፡ ድል ፡ እንዳደረጉ ፡ በአንክሮ ፡ ሲወራ አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ እኔስ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ ጥላዋ ፡ እስክታልፍ ፡ ጀንበር ፡ እስክትጠልቅ ፡ በአምላኬ ፡ ታግዤ በሚሰጠኝ ፡ ጸጋ ፡ የጸድቅን ፡ ጐዳና ፡ እስከጫፍ ፡ ተጉዤ ቃል ፡ እንደገባልኝ ፡ ለእረፍት ፡ ሲጠራኝ ፡ አክሊል ፡ ቢጠብቀኝ ከሁሉም ፡ የሚበልጥ ፡ የነፍሴ ፡ መድኃኒት ፡ ፊት ፡ ነው ፡ የሚናፍቀኝ አዝ:- እኔ ፡ በበኩሌ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ ተጠማሁኝ ፡ ያለው ፡ የደሙ ፡ ፍሬ ፡ ነኝ እኔን ፡ ብትጠይቁኝ ፡ የኔ ፡ ነው ፡ የምለው ፡ ምንም ፡ ታሪክ ፡ የለኝ ምህረት ፡ የተቀበልኩ ፡ ሞት ፡ የተሻረልኝ ፡ እድለኛ ፡ ሰው ፡ ነኝ